Automotive Lesson

Automotive Lesson 3

የነዳጅ መኪና ወይስ የኤሌክትሪክመኪና???የነዳጅ መኪና ወይስ የኤሌክትሪክመኪና???
የዛሬዉ ትምህርት ስለ ኤሌክትሪክ መኪና ካብራራዉት ዉስጥ በዉስጥ መስመር የተጠየኳቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ እሞክራለሁ
ጥያቄ ቁጥር.ቁ 1 ፡-የኤሌክትሪክ መኪናዎች ከነዳጅ መኪናዎች አንጻር ምን ምን አላቸው?
ባለንበት በዚህ ግዜ ከዘመኑ ጋር እኩል ሊራመድ የሚችል የቴክኖሎጅ ዉጤት መጠቀም ካልተቻለ ጉዳቱ በጌንዘብ እና በግዜ የሚገለፅ ይሆናል፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ታዳግ ሀገራት ኤሌክትሪካል መኪናዎች የረዥም ግዜ እቅድ ተይዞ እየተሰራበት ይገኛል፡፡ ኤሌክትሪካል እና ነዳጅ መኪናዎች ብሎ ማወዳደር ከባድ ቢሆንም እንደተጠቃምዉ አይነት ሁለቱም የየራሳቸዉ ፈላግዎች አላቸዉ፡፡ መነሻችን ነዳጅ መኪና ስለሆነ የኤሌክትሪክ መኪናዎች ከነዳጅ መኪናዎች አንጻር ምን አላቸው ምንስ ይጎድላቸዋል የሚለዉን በዝርዝር ለማየት እንሞክራለን፡፡
በኤሌክትሪካል መኪና ላይ ያሉ ጥቅሞች
አንስተኛ የመንቀሳቀሻ እና የጥገና ወጭ-የመጀመሪያዉ የኤሌክትሪክ መኪናዎች ጥቅም ለመንቀስቀስ የምናወጣዉ ወጭ አነስተኛ መሆን ነዉ፡፡ በተመሳሳይ አንድ ኪ.ሜ ለመጓዝ የምንጠቀመዉ ነዳጅ እና የኤሌክትሪክ ዋጋ እስከ ሶስት እጥፍ ሊቀንስ ይችላል፡፡ በተጨማሪም ኤሌክትሪካል መኪናዎች ምንም አይነት የነዳጅም ሆነ የማለስለሻ ዘይት( Lubrication system) አያስፈልጋቸዉም፡፡ በተደጋጋሚ ሊሰበሩ የሚችሉ የሞተር ክፍልም ሆነ ጥርሳጥርስ ስለሌላቸዉ በተደጋጋም ልናወጣዉ የምንችለዉን የጥገና ወጭ ይቀንሱልናል፡፡
በጣም ምቹ እና ፈጣኖች ናቸዉ-በነዳጅ ተሸከሪካር ግዜ የምንሰማቸዉ የጥርሶች ፍጭት እና ኃይል ለመፍጠር የሚደረግ ማንኛዉም ሜካንካል እንቅስቃሴ በኤሌክትሪክ መኪኖች ጊዜ አይኖርም፡፡ በነዳጅ መኪኖች ላይ ሞተር ኃይል ለመፍጠር ሲሞከር እና ፒስተኖች ከላይ ወደ ታች ሲመለሱ (when the piston moves from TDC to BDC) በመኪናችን ላይ ከፍተኛ ንዝረት(vibration) ይፈጠራል፡፡ በተጨማሪም ማርሽ ስንቀይር እና ከአንዱ ፍጥነት ወደ ሌላዉ ስንሸጋገር በምንጠቀመዉ በነዳጅ እና በፍርስዮን ፔዳል አረጋገጣችን ምክንያት ከፍተኛ ንዝረት ይኖራል፡፡ ይህ ሁሉ በኤሌክትሪክ መኪና ግዜ በአንድ የፍጥነት መቆጣጠርያ ፔዳል (acceleration pedal) ብቻ ስለምተካ ፈጣን እና ምቹ ጉዞ እንድኖረን ያደርጋል፡፡ ኤሌክትሪካል መኪኖች ከዜሮ በአንድ ጊዜ 60 ኪ.ሜ በሰአት ለመብረር ከሁለት እስከ ሶስት ሰኮንድ ብቻ ይበቃቸዋል፡፡
በቤት ዉስጥ ቻርጅ መደረጋቸዉ- የኤሌክትርክ መኪኖቻችንን ቻርጅ ለማድረግ ሶስት መንገዶች አሉ፡፡ የመጀመርያዉ እንደ ማንኛዉም መኪና መንገድ ዳር ባሉ ቻርጅ ማድረግያ ጣብያዎች የምናደርገዉ ስሆን ሁለተኛዉ በቤታችን ጋርጅ ወይም ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ ቦታ ላይ በቀላሉ ቻርጅ የምናደርግበት ዘዴ ነዉ፡፡ ይህም ለሊት ለሊት ቻርጅ እያደረግን ቀን ቀን እንድናሽከረክር ይረዳናል፡፡
ከአየር ንብረት እና ከጤና ጋር ተስማሚ መሆናቸዉ- በተደረገ ጥናት መሰረት የኤሌክትሪክ መኪኖች ምንም አይነት የአየር ብክለት የማይደርሱ ወይም ዜሮ የተበከለ አየር ልቀት( zero emission) በሚል ይታወቃሉ፡፡ ለዚህም ሲባል ያደጉ ሀገሮች የኤሌክትሪክ መኪናን ለሚገዙ ሰዎች ለአከባቢ ብክለት አስተዋፆ ስለማያደርጉ በምል የታክስ (tax) ቅናሽን ጨምሮ ሌሎች እገዛዎች ይደረግላቸዋል፡፡
ሰፋ ያለ የእቃ መጫኛ ቦታ ይኖራቸዋል- ብዙ የስራ እንቅስቃሴ ላለዉ፤ የቀን ፍጆታዎችን በተደጋጋሚ ለሚገበይ እና የገዛዉን በመኪናዉ ጭኖ ለሚመለስ አሽከርካሪ የመጫኛ ቦታ ምን ያህል ችግር እንደሆነ መገንዜብ ይቻላል፡፡ በኤሌክትሪክ መኪኖች ላይ የነዳጅ ሞተር እና ካምቢዮ ስለማይኖር ሰፋ ያለ ቦታ ለእቃ መጫኛነት ያገለግላል፡፡ በተጨማሪም እነዚህ ክፍሎች አለመኖራቸዉም መኪናችን ያልተፈለገ ክብዴት እንዳይኖረዉ በአንስተኛ ኃይል እንድቀሳቀስ ያስችለዋል፡፡
ጥያቄ ቁጥር .ቁ 2፡- በኤሌክትሪክ መኪና ላይ የምነሱ ጉድለቶች ምን ምን ልሆኑ ይችላሉ?
የባትሪ ቆይታ እና የቻርጅ ቦታ- ከተወሰኑት የኤሌክትሪክ መኪና ምርቶች ዉጭ አብዘሀኞቹ ከ 120- 180 ኪ.ሜ ብቻ የመጓዝ ብቃት አላቸው፡፡ ይህ በአንድ ቻርጅ የምደረግ ጉዞ ረዥም ርቀት መጓዝ ለምፈልጉ አሽከርካሪዎች ከባዱ ፈተና ይሆናል፡፡ ምናልባትም እንደ ነዳጅ በፈለግንበት ቦታ ቻርጅ የሞምላት ቦታዎችንም ላናገኝ እንችላለን ፡፡ ይህ ብቻ ሳይበቃ መንገድ ላይ ባሉ 240 ቮልት ሙሉ ቻርጅ ለማድረግ እስከ አራት ሰዓታትን ሊዎስዲ ይችላል፡፡ በቤታችን ዉስጥ ባሉ በባለ 11 ቮልት ቻርጀሮች ሲሆን ደግሞ እስከ 10 ሰዓት መጠበቅ ግድ ይለናል፡፡
ዋጋቸዉ ዉድ ነዉ- በተመሳሳይ ብቃት እና ደረጃ ላይ ካለ አንድ የነዳጅ መኪና ጋር ቢወዳደር የኤሌክትሪክ መኪኖች ዉድ ናቸዉ፡፡ እንደ ነዳጅ መኪና በየግዜዉ የሚናወጣዉ ወጭ ባይኖረንም ባትሪዉ ከተበላሽ እና ሊያስወጣን የሚችለዉን ገንዘብ ማሰቡ ቢቀርብኝስ ሊያስብል ይችላል፡፡ እንደ Tesla ዓይነት አማራቾች ለባትሪዉ ቆይታ እስከ ስምንት አመት ዋስትና ይሰጣሉ፡፡
የተለመዱ የነዳጅ መኪና ልምዶችን ያስቀራል- አንድ የነዳጅ መኪና አሽከርካርሪ የመኪናዉ ጭስ ካልሸተተዉ መኪና ያሽከረከረ አይመስለዉም ቢባል ቀልድ ሊመስል ይችላል፡፡ ቢሆንም ግን በኤሌክትርክ መኪኖች ላይ ምንም አይነት የጭስ ተረፈ ምርት አይኖርም፡፡ በተጨማሪም ማርሽ ስቀያየር የሚሰማዉ የጩሄት ድምጽ እንደ ሙዝቃ ማዳመጥ የለመደ አሽከርካሪ የኤሌክትሪክ መኪና ለምኔ ማለቱ አይቀርም፡፡ እነዚህን ልምዶች በኤሌክትሪክ መኪና ላይ አናገኛቸዉም ፡፡ ለላዉ ጉድለት የምባለዉ በፈለግነዉ ሞዴል እና አይነት መኪኖችን ማግኘት አለመቻላችን ነዉ፡፡ @bemnetautomotive

Automotive Lesson

Automotive Lesson2

#የኤሌክትሪክ መኪና እንደት ይሰራል?

How electric car works


ስለ አንድ መኪና ዉስጣዊ ክፍል ስናስብ ሁሌም ወደ አእምሯችን ከሚመጡ ክፍሎች ዉስጥ ሞተር(engine)፤ ቮላኖ(flywheel)፤ ደብራተር( air- cleaner)፤ ሞተሪኖ( starter motors)፤ ካምቢዮ(gearbox)፤ ፊልትሮ(fuel-filter)፤ የዉኃ ፓምፕ(water-pump) እና ፍሪስዮን(clutch) ዋና ዋናዎቹ ናቸዉ፡፡ አንድ መኪና ያለ-እነዚህ ክፍሎች መኪና ሆኖ መሽከርከር ይችላል ቢባል እንደት? ተብሎ መጠየቁ አይቀርም፡፡ በነዳጅ ከሚንቀሳቀሱ መኪኖች አንፃር ኤሌክትሪካል መኪናዎች አንፃር ኤሌክትሪካል መኪናዎች እስከ 90% የሚሆን ተንቀሳቃሽ ክፍሎች ይቀንሳሉ፡፡ ይህም ማለት ኤሌክትሪካል መኪናዎች አብዘሀኞቹ ሜካንካል እንቅስቃሴ ያላቸዉን ክፍሎች በማስወገድ በተለየ እና ኤሌክትሪካል በሆኔ መንገድ ብቻ እንቅስቃሰን ያደርጋሉ ማለት ነዉ፡፡
በነዳጅ ተሽከርካሪዎች ግዜ ቁልፋችንን ስናዞር ሞተሪኖ የፍላይዌልን( ቮላኖ) ጥርስ ያዞራል ይህም በሞተር ዉስጥ ያሉ ፒስተኖች እና ክራንክ ሻፍቶች እንዲቀሳቀሱ እና ክራንክ ሻፍቶች እንድቀሳቀሱ እና ኃይል እንዲያመነጩ ያደርጋቸዋል፡፡ የተመረተዉ ኃይል ቀጥታ ወደ ጎማ መተላለፍ ስለማይችል በመካከል ካምቢዮ የምባል ኃይል አስተላላፍ ክፍል መኖሩ ግድ ይላል፡፡ ይህ ክፍል በክላች አማካኝነት ኃይል እየተቀበለ እና ሃይል እየተቋረጠበት የተመጠነዉን ሃይል በሻፍቶች አማካኝነት ወደ ዲፈረንሻል ይልካል፡፡ ዲፈረንሻልም የተቀበለዉን ኃይል በሚገባቸዉ መጠን ለጎማዎች በማከፋፈል ስራዉን ይቋጫል፡፡ ይህ የስራ ሂደት በነዳጅ ተሽከርካሪዎች ዉስጥ የምገኝ የስራ ሂደት በነዳጅ ተሽከርካሪዎች ዉስጥ የምገኝ የስራ ሂደት ነዉ፡፡ ይህንን አይነቱ የስራ ቀደም-ተከተል ግን በኤሌክትሪክ መኪና ላይ አይገኝም፡፡
የኤሌክትሪክ መኪኖች(EVS) የምሰሩት ቻርጅ በመደረግ ሲሆን በዉስጣቸዉ ባለዉ Lithium-ion batteries አማካኝነት ኃይል ይሰበስባሉ፡፡ የሰበሰቡትን ኃይል የነዳጅ ሃይል የነዳጅ ቦታን በመተካት ሙሉ የመኪናችንን እንቅስቃሴ ይሸፍናል፡፡ በዚህም መሰረት በኤሌክትሪክ መኪና ላይ የተገጠመዉ የነዳጅ ሞተር ሳይሆን Elecrtic Motor ይሆናል፡፡ ይህ ማለት የነዳጅ ማጠራቀሚያ ቋት(fuel-tank) አይኖረዉም በተቃራኒዉ በመኪናችን የፊት እና የኋላ ጎማ መካከል ባለዉ ታችኛዉ ክፍል እስከ 7000 የሚደርሱ Lithium-ion ባትሪዎች ተደርድረዉ ይገኛሉ፡፡ የመኪናችሁን ኮፈን ከፍታችሁ አንድ እቃ መቀየር ብትፈልጉ ምን ያህል ገመዶችን እና ሆስ(ማንኮቶ) መፍታት ወይንም ማንቀሳቀስ እንዳለባችሁ የምታዉቁት ነዉ፡፡ በኤሌክትሪካል መኪና ጊዜ የምቀዘቅዝ ሞተርም ሆነ ወደ ሞተር የምሄድ የሴንሰሮች ገመድ ስለማይኖር የኤሌክትርክ መኪናን የፊተኛዉን ኮፈን የምንከፍተዉ እቃ ለመጫን ብቻ ነዉ፡፡
በኤሌክትሪካል መኪና ዉስጥ ያለዉ የባትር ጥርቅም ኃይል የሚሰበስበዉ በ DC (Direct current) መልክ ነዉ፡፡ ይህ ኃይል እንደምታወቀዉ one direction (በአንድ አቅጣጫ አንድ አይነት ኃይል የሚያስተላልፍ) ነዉ፡፡ ስለዚህም ይህን ኃይል ወደ AC (Alternating Current) የሚቀይርልን ክፍል ኢቨርተር (inverter) ይባላል፡፡ ኢቨርተር የተመጠነዉን እና መቆጣጠር የምንችለዉን ኃይል ወደ induction motor (ሞተር) ያስተላልፋል፡፡ ሞተራችን የተቀበለዉን ኃይል ወደ ጎማችን በመላክ መኪናችን መንቀሳቀስ እንዲችል ያደርጋል፡፡
የኤሌክትሪካል መኪናዎችን ከሚያስተቻቸዉ ነገሮች ዉስጥ አንዱ ባትሪ ቻርጅ ለማድረግ የሚወስደዉ ጊዜ ነዉ፡፡ ቻርጅ በሶስት አይነት መንገድ ማድረግ የሚቻል ሲሆን የመጀመሪያዉ በቤታችን ዉስጥ የምናደርገዉ ነዉ፡፡ ሌላዉ በቻርጅ ጣቢያዎች የሚደረግ ሲሆን ሶስተኛዉ በልዩ ሁኔታ በ DC ቻርጅ የምናደርግበት መንገድ ነው፡፡ እንደየደረጃቸዉ ፈጣን የመሙላት አቅም ሲኖራቸዉ በ DC ቻርጅ የማድረጉ ሂደት እጂጉን ፈጣን እና ጊዜ ቆጣቢ ነው፡፡
ለምሳሌ አንድ የ Tesla S ሞደል መኪና ሙሉ ቻርጅ ለማድረግ እስከ 10 ሰዓት ሊወስድበት ይችላል፡፡ ይህ በአንድ ሙሉ ቻርጅ ደግሞ ከ 350-400 km እንዲጓዝ ያስችለዋል፡፡ ነገር ግን አብዘሀኞቹ የኤሌክትሪክ መኪና ምርቶች ከ 120-180 km ርቀትን ብቻ የማስጠቀም አቅም አላቸዉ፡፡ በተጨማሪም ፍሬን ፔዳላችንን በምንረግጥበት ግዜ የሞተራችን እሽክርክሪት በተቃራን አቅጣጫ ይሆናል፡፡ ይህ ሂደት ሞተራችንን ከኃይል አስተላላፊነት(electric motor) ወደ ኃይል አመንጭነት(electric generator) በመቀየር ባትሪያችን ቻርጅ እንድሆን ያደርጋል፡፡ ይህ ሂደት regenerative brakes ሲባል በትንሹም ቢሆን ከመኪናችን ኃይል እንድናገኝ ያስችለናል፡፡
copyright@bemnetautomotive

Automotive Lesson

Automotive Lesson1

The most common car warning lights❗️

 1. Fog light (front)
 2. Power steering warning light
 3. Fog light (rear)
 4. Washer fluid low
 5. Brake pad warning
 6. Cruise control on
 7. Direction indicators
 8. Rain and light sensor
 9. Winter mode
 10. Information indicator
 11. Glow plug/diesel pre-heat warning
 12. Frost warning
 13. Ignition switch warning
 14. Key not in the vehicle
 15. Key fob battery low
 16. Distance warning
 17. Press clutch pedal
 18. Press brake pedal
 19. Steering lock warning
 20. Main beam headlights
 21. Tyre pressure low
 22. Sidelight information
 23. Exterior light fault
 24. Brake lights warning
 25. Diesel particulate filter warning
 26. Trailer tow hitch warning
 27. Air suspension warning
 28. Lane departure warning
 29. Catalytic converter warning
 30. Seat belt not on
 31. Parking brake light
 32. Battery/alternator warning
 33. Parking assist
 34. Service required
 35. Adaptive lighting
 36. Headlight range control
 37. Rear spoiler warning
 38. Convertible roof warning
 39. Airbag warning
 40. Handbrake warning
 41. Water in filter
 42. Airbag deactivated
 43. Fault problem
 44. Dipped beam headlights
 45. Dirty air filter
 46. Eco-driving indicator
 47. Hill descent control
 48. Temperature warning
 49. ABS warning
 50. Fuel filter warning
 51. Door open
 52. Bonnet open
 53. Low fuel
 54. Automatic gearbox warning
 55. Speed limiter
 56. Suspension dampers
 57. Oil pressure low
 58. Windscreen defrost
 59. Boot open
 60. Stability control off
 61. Rain sensor
 62. Engine/emissions warning
 63. Rear window defrost
 64. Auto windscreen wiping
PreviousNext

You Want To Have Your Favorite Car?

We have a big list of modern & classic cars in both used and new categories.